top of page
Search

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ።

Writer: kambattomai
kambattomai
Sep 12, 2023
1 min read

ውድ የከምባቶማ አክሽን ዓለምአቀፍ ድርጅት (ፎረም) አባላት በሙሉ፣ ደጋፊዎች፣ ወዳጆች፣ መላው የከምባታና የሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ፥ ከምባቶማ አክሽን ዓለም አቀፍ ድርጅት እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ ይላል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የደስታ፣ አብሮነትና መቻቻል የሚታይበት፣ መልካም ዕሴቶቻችን የሚለመልሙበት፣ ኋላ ቀርነት፣ ድህነት፣ መከራ፣ ችግር፣ ረሃብና ጦርነት የሚቀረፉበት፣ ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚገባበት፣ ሌብነት፣ ሙስና፣ ዝርፊያ የሚያበቃበት፣ እሾክና አሜከላ የሚነቀልበት፣ በሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና የሚታይበት፣ የልማት ማነቆዎች የሚወገዱበት፣ አንድነትና እኩልነት ተዘርቶ የሚታጨድበት፣ የሚያድጉበት፣ በውጤቶቻቸውም እንደ ሕዝብ የምንገለገልበት፣ የምንለወጥበትና የምናድግበት እንዲሆን ከምባቶማ አክሽን ዓለም አቀፍ ድርጅት (ፎረም) ይመኛል።

መልካም 2016 አዲስ ዓመት ይሁንልን!

September 11, 2023


 
 
 

Recent Posts

See All
KAIF's Open Letter to South African Government

በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ አፍሪካውያንና ኢትዮጵያውያን ወገኖች ላይ እየተካሄደ ያለው የጥላቻ፤ የጥቃት፤ የዘረፋ፤ የንብረት ቅሚያና ግድያ ተግባሮች እንድቆሙ፤ ይህን ድርጊት የሚመሩ ቡድኖችና ግለሰቦች በሕግ እንድጠየቁ፤ እንዲሁም የሲሪል ራማፎሳ መንግሥት በአስቸኳይ የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር ጥሪ የሚያደርግ ግልጽ

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page